የኢትዩጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ETHIOPIAN AGRICULTURAL BUSINESSES CORPORATION


slide-1 2 3

የሕዝብ ድርጅት ሚኒስቴር

የኢትዮጵያ የግብርና ቢዝነስ ኮርፖሬሽን

በ ኮርፖሬሽን አርማ መግቢያ ተሰታፊዎች

አንድ ንግግር በሚያቀርብበት ጊዜ ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር

ስለኛ

አመሰራረት

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ቀደም ሲል የኢትዮጵያ ምርጥ ዘር ድርጅት፣ የእርሻ መሣሪያዎችና የቴክኒክ አገልግሎት አክስዮን ማህበር፣ የግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅራቢ ድርጅት፣ የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት ድርጅት፣ የተፈጥሮ ሙጫ ምርትና ገበያ ድርጅት የተባሉ አምስት የመንግስት የልማት ድርጀቶችን በማዋሀድ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 368/2008 ከታህሣሥ 12 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ የተቋቋመ መንግስታዊ የልማት ድርጅት ነው።

ተግባርና ሀላፊነቶች

የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፓሬሽን የሚከተሉት ተግባርና ሀላፊነቶች አሉት።

የግብርና ምርት ማሣደጊያዎች ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር ገዝቶ ለገበያ ማቅረብ፤ ማዘጋጀት፤ የግብርና ምርት ማሳደጊያዎችን ገበያ ማረጋጋት ተግባርን ማከናወን፤

የግብርና ሜካናይዜሽን አገልግሎት፤ የእርሻና የኮንስትራክሽን መሣርያዎች የጥገና አገልግሎት፤ የእርሻ መሣርያዎችንና የትራንፖርት ተሽከርካሪዎትን የኪራይ አገልግሎት መስጠት፤

የእርሻ መሣርያዎችን፤ የኮንስትራክሽን መሣርያዎችን እና አግሮ ኬሚካሎችን ከሀገር ውስጥና ከውጪ ሀገር ገዝቶ ለሽያጭ ማቅረብ፤

ዘመናዊ የአርሻ መሣርያዎችን አጠቃቀም እንዲለመድ አስፈላጊውን ሥልጠና መስጠት፤ ስለ እርሻ መሣርያዎች አያያዝና አጠቃቀም የምክር አገልግሎት መስጠት፤ ስለ እርሻ መሣርያዎች አያያዝና አጠቃቀም የምክር አገልግሎት መስጠት፤ የቴክኒክ ሙያ ማሻሻያ ሥራ ሥልጠና መስጠት

የተፈጥሮ ሙጫ ምርት መሰብሰብ፤ መግዛት፤ እሴት መጨመር፤ ማዘጋጀት፤ ሌሎች ከደን ውጤቶች የሚመረቱ ምርቶችን ማምረት፤ ለሀገር ውስጥና ለውጪ ገበያዎች ማቅረብ፤

ቅድመ መስራች ዘሮችን ማባዛት እና ምርጥ ዘሮችን ማበጠር፤ ማዘጋጀትና ማከፋፈል እና

ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተዛማጅ ሥራዎችን መሥራት

 

ምርት እና አገልግሎታችን

የኮንስትራክሽን እና የትራንስፖርት መሣሪያዎችን ማከራየት

የደን ልማት፣ የተፈጥሮ ሙጫ ምርቶችና ሌሎች የደን ውጤቶችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ገበያ ማቅረብ

የመሬት ልማትና ሜካናይዜሽን አገልግሎት

የአፈርና የአበባ ማዳበሪያዎች

የግብርና ግብዓት አቅርቦት ኢንተርፕራይዝ

ኤ. ም. ኤስ. ኢ

የእርሻ መሣሪያዎች የቴክኒክ አገልግሎት

የተፈጥሮ ሙጫ